ዝክረ ፋሲካ – 2000

XNµ*N lBR¦n TNœx@W bs§M xdrúCh#ÝÝ  

Melkam Fasika 

 

 

 

„ሰኞ መከሩ፣ ማክሰኞ ዘከሩ
ሮብ ዶለቱ፣ ኀሙስ አገቱ
አርብሳ ሰቀሉታ፣
እሑድሳ
እንጣጥ ብሎ ተነሣ
ጌታዬ አንበሳ፡፡
ዓመታዊው ግን ተዘዋዋሪው የፋሲካ (ትንሣኤ) በዓል በመጣ ቁጥር እየተፈጠሩ ካለፉት ሥነቃሎች አንዱና በቆሎ ተማሪዎች ዘንድ በኅብረ ዝማሬ ይቀርብ የነበረ ነው፡፡ ትንሣኤ በክርስቲያኖች ዘንድ ታላቅ ክብረ በዓል ሆኖ ይታያል፡፡ በሚከተሉት ሥርዓተ ዘመን አኳያ ምዕራባውያኑ ከአራት ሳምንታት በፊት (መጋቢት 14) ያከበሩት ሲሆን ምሥራቃውያኑ ኦርቶዶክሳውያን ኢትዮጵያና ኮፕትን (ግብጽ) ጨምሮ በዛሬው ዕለት (ሚያዚያ 19 ቀን 2000 .) ያከብራሉ፡፡
 ኢትዮጵያውያኑ ኦርቶዶክሳውያን ፋሲካን የሚያከብሩት 55 ቀናት ያሳለፉትን የጾም ወራት በማጠናቀቅ ነው፡፡ ጾሙዐቢይ ጾምወይምሁዳዴተብሎ የሚታወቅ ሲሆን ከሥጋና ከወተት ተዋጽኦና ከልዩ ልዩ ነገሮች በመታቀብ ሁዳዴውን አሳልፈውታል፡፡ 
ምሥራቃውያኑ በጾም የቆዩት 46 ቀናት መነሻቸውአሽ ዌንስዴይበሚሉት ዕለተ ረቡዕ ሲሆን፣ የኢትዮጵያና ኮፕት ግን ከሰኞ የሚብት ነው፡፡ በአገሪቱ የጾም ባህል መሠረት 55 ቀን የሆነው አንዳንዶች ያለ ዕውቀት እንደሚሉት 15 ቀንየንጉሥ ጾምሳይሆን የመጀመሪያው ሰባት ቀን ቅዱስ ያሬድ እንዳለው ዘወረደ፣ ሙሴኒ (የመዘጋጃ ጾም) በኋላ የታከለውን ንጉሥ ሕርቃልን ትተን፣ የመጨረሻው ስምንት ቀናት ደግሞ ሰሙነ ሕማማት ተብሎ የሚታወቅ ነው፡፡ 
 
በእሑድ ፋሲካ ዋዜማ ቀዳም ሥዑር (ቅዳሜ ሹር) በዓል ሲሆን፣ ቄጠማ እየታደለገብረ ሰላመ በመስቀሉ ወአግሀደ ትንሣኤሁ“ (በመስቀሉ ሰላምን አደረገ፤ ትንሣኤውም ግልጽ ሆነ) ተብሎ ይከበራል፡፡ ምሽት ላይ ምእመናን ወደየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናቸው ጧፍና ሻማ በመያዝ በምሥራቹና በሥርዓተ ቅዳሴው ለመካፈል የሚጓዙበት ነው፡፡ እስከ መንፈቀ ሌሊት ይቆያሉ፤ ዶሮ ሲጮህ ይፈስካሉ፤ 
የቅዱስ ያሬድ ማኅሌታይ ድርሰት የሆነው የትንሣኤ ምልልስ የበዓሉ መለያ ነው፡፡ እንዲህ ይላሉ፤ 
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታንክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣንበታላቅ ኃይልና ሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣንሰይጣንን አሰረው
አግአዞ ለአዳምአዳምን ነፃ አወጣው
ሰላምሰላም
እምይእዜሰከዚህም በኋላ
ኮነ ፍሥሐ ወሰላም“ – ፍሥሐና ሰላም ሆነ
 
የምሥራች ቃለ ምልልሱ በትንሣኤ ሳምንት ሁሉ ካህናትና ምዕመናን ሲገናኙ የሚለዋወጡት በትንሣኤ ወቅት ብቻ የሚከሰት የሰላም ገጽታ ነው፡፡ 
ለምእመናኑ በመንፈሳዊ እርሻ የተመሰለው ሁዳዴው ሲጀመር
ጀግናው ዐቢይ ጾም ቢታይ ብቅ ብሎ፣
ቅቤ ፈረጠጠ አገር ርስቱን ጥሎተብሎ በሕዝባዊ ሥነቃል (ቃል ግጥም) የታጀበው ጾም ሲፈታ፣ በተለይ ሌሊት ዘጠኝ ሰዓት ላይ ከቅባት የተለየው አካል እንዳይጎዳ ልዩ ምግብ ይዘጋጅለታል፡፡ ማለስለሻ እንዲሆን ተልባ ይቀርባል፡፡ በጸሎተ ኀሙስ ዕለትም ለየት ያለ የምግብ ባህል አለ፡፡ ጸዋሚዎቹ ጉልባንና ንፍሮ ቀምሰው እስከ ትንሣኤ ሌሊት ሳይመገቡ ያከፍላሉ፡፡ ጉልባን ባቄላ፣ ስንዴና ጥራጥሬ ተቀላቅሎበት የሚዘጋጅ የምግብ አይነት ነው፡፡ ዓርብ ስቅለት ከስግደት መልስም ጉልባን ይበላል፡፡ የሐዘን መግለጫ ሆኖ ተወክሏል፡፡
እንደየኅብረተሰቡ ባህል የፋሲካ ድፎ ዳቦ፣ ዶሮ ዳቦ፣ ኅብስት፣ የዶሮ ወጥ እንቁላል፣ የእርድ ከብቶችን ማዘጋጀት ጠጅና ጠላ መጠጥ ማዘጋጀት የክብረ በዓሉ አንዱ ገጽታ ነው፡፡ ከመልካም ምኞቱ እንኳን አደረሳችሁ፣ ጾመ ልጓሙን እንኳን ፈታልዎ በአነጋገር ደረጃ የሚጠቀስ ነው፡፡ ከርቀትም ሆነ ከቅርበት ያሉ ቤተሰቦች የሚሰባሰቡበት ስጦታ ሙክት፣ ድፎ ዳቦና መጠጦች የሚለዋወጡበትም ነው፡፡ 
ትንሣኤ በትውፊታዊ ትእምርቶችና አይቆኖች (ICONS) ምስልና ቅርጾች ይታጀባል፡፡ በምሥራቁም ሆነ በምዕራቡ ዓለም የሚታዩ አንዳንድ የትንሣኤ ትእምርቶች መነሻቸው ከቅድመ ክርስትና በፊት ከነበሩት ልማዶችና የአሕዛብ እምነቶች ምልክቶችን በሚስማማ መልኩ የቀረበበት ነው፡፡ ጥንቸልና በልዩ ልዩ ቀለማት ያሸበረቁ እንቁላሎች ሲጠቀሱ የትንሣኤ መስቀልና ነጭ አበባ ስቅለቱን ወክለው ይታያሉ፡፡ 
የትንሣኤ በዓል አከባበር በአቆጣጠር ልዩነት የተነሣ 16ኛው ምእት በኋላ ምሥራቆችና ምዕራቦች ከመለያየታቸው በፊት 326 እስከ 1582 ድረስ 325 በተካሄደው ኒቅያ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት ክብረ በዓሉ በተመሳሳይ ቀን ይውል ነበር፡፡ 
በዓሉ ምንግዜም ቀኑና ሌሊቱ ትክክል ከሚሆንበት (ዕሪና መዓልት ወሌሊትኢኰኖክስ) መጋቢት 25 (በጁሊያን ማርች 21) በኋላ፣ ከአይሁድ ፍሥሕ (ፋሲካ) በኋላ፣ ባለው እሑድ ሁልጊዜ እንዲውል ይደነግጋል፡፡ ከጥቅምት 1575 . (1582) በኋላ የጁሊያን አቆጣጠርን ያሻሻለው የጎርጎርዮስ ቀመር በአብዛኛው የአውሮፓ ካቶሊኮች ተቀባይነት በማግኘቱና በተፈጠረው የቀናት መሳሳብ ሌላ የትንሣኤ በዓል ሊፈጠር ችሏል፡፡ 
የኦርቶዶክስ ፋሲካ የጁሊያንን ቀመር፣ ኢትዮጵያና ኮፕት ደግሞ በራሳቸው ቀመር የኒቅያውን ድንጋጌ ይዘው በመዝለቃቸው ክብረ በዓሉን በአንድ ቀን ያከብራሉ፡፡ በኢትዮጵያና በኮፕት ባሕረ ሐሳብ መሠረት የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ዓርብ መጋቢት 27 ቀን፣ ትንሣኤው እሑድ መጋቢት 29 ቀን 34 . የዋለ ሲሆን፣ በየዓመቱ እነዚህ ዕለታት ጥንተ ስቅለት፣ ጥንተ ትንሣኤ ተብለው በስንክሳር መሠረት ይታሰባሉ፡፡ ትንሣኤ በየ95 ዓመቱ በአመዛኙና በተቃርቦ በዋለበት ይውላል፡፡ 
ትንሣኤን ተከትለው ቀናቸው በየዓመቱ የሚዘዋወሩት አጽዋማትና በዓላት የአወጣጥ ሥርዓት መደበኛውን ፀሐያዊ አቆጣጠር ሳይሆን የፀሐይና ጨረቃን ጥምር አቆጣጠር (ሉኒሶላር) ይከተላል፡፡ ይህም በመሆኑ ትንሣኤበዓላትበተባለው የብርሃኑ አድማስ መጽሐፍትንሣኤ ከመጋቢት 25 አይወጣም፣ ከሚያዚያ 29ኝም አይወርድምተብሎ በስህተት እንደተጻፈው ሳይሆን በመጋቢት 26 እና በሚያዚያ 30 መካከል ባሉት 35 ቀናት ውስጥ እንዲውል ይደረጋል፡፡ 

ጥንታዊ መጽሐፍ ፍትሐ ነገሥት በፍትሕ መንፈሳዊ ክፍሉ ሰለ ትንሣኤ በዓል አከባበር እንዲህ ይላል፡፡የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤውን በዓል በዕለተ እሑድ እንጂ በሌላ ቀን አታድርጉ፤ በመንፈቀ ሌሊት ብሉ፤ ያም ባይሆን በነግህ ብሉ. . . ከዚህም በኋላ ፈጽሞ ደስ እያላቸሁ ጾማችሁን በመብል በመጠጥ አሰናብቱ፤ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቷልና፤

ከትንሣኤ በፊት ያሉት ሰሙነ ሕማማትና ዓርብ ስቅለት በተለይ በጾምና በስግደት የሚከበሩ ናቸው፡፡ በወይራ ቅጠል ጥብጠባ በማሳረጊያው ይደረጋል፡፡ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ትውፊትና ሥርዓት መሠረት ከሆሳዕና ሰኞ እስከ ጸሎተ ኀሙስ ያሉት ቀናት ከክርስቶስ ልደት በፊት የነበሩትን 5500 ዓመታት (አምስት ተኩል ቀናት) „የዓመተ ፍዳመታሰቢያ ሆነው ተሠርተዋል፡፡ 
    
ከትንሣኤ አንድ ሳምንት በፊት እሑድ የሚከበረው ሆሳዕና ባህላዊ ገጽታዎች የሚታዩበት ነው፡፡ በሁሉም የአገሪቱ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ዐውደ ምሕረት ምእመናኑ እየተገኙ የዘንባባ ዝንጣፊ ከመያዝ ባሻገር፣ ከልሂቅ እስከ ደቂቅ በዘንባባው ቅጠል ለጣታቸው ቀለበት፣ ለእጃቸው እንደ አልቦ፣ ለራሳቸው እንደ አክሊል የሚጠለቅ አድርገው ያዘጋጃሉ፡፡ በሆሳዕና እሑድ ኢየሱስ በአህያ ውርንጭላ ላይ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁነት በማስታወስ በአንዳንድ አድባራት ተመሳሳይ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ትርዒቱ የተካሄደው 102 ዓመት በፊት ነበር፡፡ ብላታ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስየዘመን ታሪክ ትዝታዬ በዳግማዊ ምኒልክ ዘመነ መንግሥትበሚለው የትዝታ ድርሳናቸው እንደጻፉት የሆሳዕና በዓል በአክሱም ሥርዓት ዓይነት ሆኖ እንጦጦ ላይ ሊከበር የተጀመረው 1898 . መጋቢት 30 በሆሳዕና ዕለት ነው፡፡ ከአክሱም የመጡ አንድ መምህር ከበዓሉ ቀን ቀደም ብለው ጀምረው የሥነ ሥርዓቱን አፈጻጸም ለደብሩ ካህናትና ለሕፃናት መዝሙር አስጠንተዋል፡፡
በበዓሉ ዕለት አንዲቱን የበቅሎ ግልገል በወርቅ ጥልፍ የተለጠፈ ባለመረሻት (የበቅሎ የማዕርግ ልብስ፣ በልዩ ልዩ ሐሮች ተጠልፎ የተዘጋጀ ወርቀ ዘቦ) ኮርቻ ተጭኖባት ድባብ ደብበውላትና አጅበዋት ወደ ቤተክርስቲያን አመጡዋት፡፡ ዑደት ተደረገ፡፡ ከአክሱም የመጣው የሆሳዕና በዓል ሥነሥርዓት ጃንሆይ ዳግማዊ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ መኳንንትም ሁሉ ባሉበት መከበሩ ተመዝግቧል፡፡
 
       

 የትንሣኤ በዓል እስከ ዳግማይ ትንሣኤ ሳምንቱን በልዩ ስያሜ ይከበራል፡፡ በፋሲካ ሌሊት የምሥራቹን ጧፍና ሻማ በመለኮስ በቤተ መቅደሱ ዙሪያ የሚደረገው ዑደትትንሣኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ፈኑ ዲቤነ“ (ትንሣኤህን ላመንን ለእኛ ብርሃንህን ላክልን) በሚለው ዝማሬ የታጀበ ነው፡፡

ትንሣኤ በሁለተኛ ስሙ ፋሲካ ላይ ትኩረት የሚያደርጉ ብሒሎችም አሉ፡፡
ፋሲካን ሊያገኙ ሁዳዴን ይመኙ፤
ሳይጾሙ ፋሲካ፣ ሳያዝኑ ደስታ የለም፤
ፋሲካ የሌለው ጦም፣ ደስታ የሌለው ዓለም፤
በፋሲካ የተገዛች ባሪያ ሁሌ ፋሲካ ይመስላታል፤
ሁሌ ፋሲካ የለም፤ ተጠቃሾች ናቸው፡፡
 
በኢትዮጵያ አዲሱ ሦስተኛው ሺሕ ዓመት፣ ትንሣኤ (ፋሲካ) ሚያዚያ 11 ቀን 2001 . ይውላል፡ በባህላችን ባለው መልካም ምኞት   

እንበለ ደዌ ወሕማም
እንበለ ጻማ ወድካም
ዓመ ከመ ዮም ያብጽሐኒ፣ ያብጽሕክሙ
እግዚአብሔር በፍሥሐ ወበሰላም
 

ያለደዌና ሕማም፣ ያለ ጻማና ድካም እንደ ዛሬው ሁሉ ለከርሞ እግዚአብሔር በደስታና በሰላም ያድርሰኝ፣ ያድርሳችሁ፡፡
ሄኖክ ያሬድ

 

 

 

Advertisements
von Bete Mariam Veröffentlicht in News

Kommentar verfassen

Trage deine Daten unten ein oder klicke ein Icon um dich einzuloggen:

WordPress.com-Logo

Du kommentierst mit Deinem WordPress.com-Konto. Abmelden /  Ändern )

Google+ Foto

Du kommentierst mit Deinem Google+-Konto. Abmelden /  Ändern )

Twitter-Bild

Du kommentierst mit Deinem Twitter-Konto. Abmelden /  Ändern )

Facebook-Foto

Du kommentierst mit Deinem Facebook-Konto. Abmelden /  Ändern )

w

Verbinde mit %s